top of page

(በያሬድ እስቲፋኖስ ዩሙራ) ጠቅላይ ሚንስትሩ የ 2.3 million ህዝብ ድምፁ ለማጠፍ እየሰራ ነው!! ==============================

(በያሬድ እስቲፋኖስ ዩሙራ)

ጠቅላይ ሚንስትሩ የ 2.3 million ህዝብ ድምፁ ለማጠፍ እየሰራ ነው!! ==============================

ጠቅላይ ሚንስትሩ የ 2.3 million ህዝብ ድምፁ ለማጠፍ እየሰራ ነው። እንዲህ አይነት አይን ያወጣ እብሪት እኔ ነኝ ያለ አምባገነን መሪ እንኳን ደፍሮ ሚሞክር አይመስለኝም ነበር።

ጠሜው ከደቡብ ክልል ከተወጣጡ ግለሰቦች ጋር ያደረገው ስብሰባ ላይ "የሲዳማ ህዝብ ወሰነ እንጂ እኛ አልወሰንም" ሲል ያው ማይክ ሲይዝ የሚቀባጥረው ነገር ስላለ ዝም ብሎ እየቀባጠረ መስሎኝ ነበር። ነገሩ ግን እውነት እየመሰለ ነው።

ወሳዕናን፣ ሶዶን፣ አርባምንጭን፣ ቦንጋን እና ሃዋሳን ማዕከላት በማድረግ ደቡብ ክልልን በ አምስት የመክፈል ሃሳብ እንዳቀረቡ ሰምቻለሁ።

የሲዳማ ሪፈረንደም ውጤትንም በመሻር ዞኑ ከአራት ኪሎ በሚላክ ክላስተር አደረጃጀት ውስጥ እንዲገባ እንደሚፈልጉ ታውቋል። በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 47 ቁጥር 3 መሰረት ሲዳማ already ክልል የሆነ ሲሆን ፤ ይህ የጠሜዉ ተግባር የተመሰረተ ክልልን በማን አለብኝነት እንደማፍረስ ነው። ይህን የሚቀባል አንድ ሲዳማ ይኖራል ማለት ዘበት ነው። *************************** ሌላው እንዲህ irrational የሆነ ስሌት በማስላት የሪፈረንደም ውጤን ለማጠፍ የሚሞክር መሪ ከስድስት ወር በኻላ በምርጫ ቢሸነፍ በሰላም ስልጣን ይለቃል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ስለዚህ plan B መያዝ የግድ ነው።

(ግብፅ እና ሱዳን ላይ እንዳየነው እኛጋም ሃገሪቱ መሉ ለሙሉ ወታደሩ እጅ የመግባት ዕድል ሊኖራት ስለሚችል፤ እኔ የምፀልየው የማደርገው ሚሊተሪዉ እንደሌሎቹ ጠቋማት ያልተቦረቦረ Intact እና disciplined እንዲሆን ነው።) ************************* ሲዳማን በሚመለከት ስሌቱ "ህዝቡን በኮማንድ ፖስት አሽተነዋል፣ ሙሁራኑን እና አክቲቪስቱን አስረናል፣ አመራሩን ከስልጣን አባረን እና ፊት ነስተን አሸማቀነዋል ፤ ስለዚህ የህዝቡ ሞራል ስለተመታ ምንም ብንወስን ይቀበላል" የሚል ነው። ይህ የቀሽም ስሌት ነው። ህዝቤ በተለያዩ ሰላማዊ ትግሎች ድምፁን እንደሚያስከብር እርግጠኛ ነኝ። ************** ሲጠቃለል...

ሲዳማ ላይ ምን መደረግ አለበት??

ዛሬ ነገ ሳይባል በፍጥነት የስልጣን ርክክብ የካሄድ። የፈደራል መንግስት አያገባውምና የጠቅላይ ሚንስትሩን ቡራኬ መጠበቅ ይቁም። አመራሮቹ ስድስት ሚሊየን ህዝብ እንደሚመራ አካል ይሁኑ። ከህዝባቸው ጎን ከቆሙ(ከቆሙለት ህዝብ የሚመነጭ) ትልቅ አቅም አላቸውና አቅማቸውን ይወቁ። አንድነታቸውን ይጠብቁ። ህዝቡን ያደራጁ። መሽቆጥቆጥ ያቁሙ።

እንደዚያ ማድረግ የማይችሉ ከሆነና የአቅም ማነስ ካለባቸው ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ ግለሰቦችን ያቀፈ ኮሚሽን(ባላደራ መንግስት) ይቋቋምና ስልጣን ይረከብ፣ መዋቅር የመዘርጋት ስራም ይስራ። ይህ ባላደራ መንግስት ከምርጫ በኻላ በህዝብ ለሚመረጥ አካል ስልጣን ያስረክብ።

ህዝቡም የባላደራ መንግስት እንዲቋቋም ፣ የስልጣን ርክክብ እንዲካሄድ ፣ የታሰሩ ሙሁራን እንዲፈቱ እና ኮማንድ ፖስት እንዲነሳ ፊት ለፊት ትግል ይጀምር ። ይኼው ነው።

Comments


Dhiyaadha odeeffannoof 
Uummata Oromoo
Archive
Search By Tags
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
bottom of page